Tao Te Ching Translation in Amharic - Part 2
Transcribed from Wisdom Ethiopia Amharic Podcast By Bisrat
AI Transcribed from here: Tao Te Ching Part 2
Please support the creator here: Wisdom Ethiopia YouTube
ምዕራፍ ፳፰–፶፬ ፳፰ ወንዱን እወቅ — ነገር ግን የሴቷን ሚና ጠብቅ። ወንዝ ሁን እና ከሰማይ በታች ያሉትን ሁሉ ተቀበል። ወንዝ ከሆንክ በጎነትህ ያላማቋረጥ ወደ አንተ ይፈሳል። ወደ ልጅነት ቅን ልቦናም ይመልስሃል። ክብርህን እወቅ — ውርደትን ጠብቅ — እና ለአለም አርአያ ሁን። የአለም አርአያ መሆን ማለት በተትረፈረፈ በጎነት ኖሮ ገደብ ወደሌለው ሁኔታ መመለስ ነው። ያልተቀረጸ እንጨት ሲቀረጽ ወደ እቃነት ይለወጣል። ጠቢቡም ጥቅም ላይ ሲውል እሱ የባለስልጣናት ሀላፊ ይሆናል። በእውነትም ድንቅ ቅርጽ ከአንድ ግንድ ተቀርጾ ይወጣል።1 ፳፱ አለምን ለመቆጣጠር የሚፈልግ ተሳክቶለት አያውቅም። ለምን ቢባል — ከሰማይ በታች ያለው ሁሉ የተቀደሰ ነው። ምንም መደረግ የለበትም። እሱን ለመቆጣጠር የሚሞክር — ያበላሸዋል። ሊይዘው የሚሞክር — ያጣዋል። ስለዚህ ህይወትህን ከተፈጥሮ ጋር የተቆራኘ እንዲሆን ፍቀድ። ይህን ማድረግ ደግሞ ወደ ሙሉነት እንደሚወስድ እወቅ። ልክ ወደ ውስጥ እና ወደ ውጪ እንደምትተነፍሰው እስትንፋስ — ለመቅደምም ጊዜ አለው ወደ ኋላ ለመቅረትም ጊዜ አለው። ለመንቀሳቀስም ጊዜ አለው ለእረፍትም ጊዜ አለው። ለጥንካሬም ጊዜ አለው ለድካምም ጊዜ አለው። ለደህንነትም ጊዜ አለው ለአደጋም ጊዜ አለው። የጠቢቡ ህይወት ወደ ሙሉነት ለመምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ ከመጠን ያለፈ እና ከልክ ያለፈ ጽንፈኝነትን ከህይወቱ ያሶግዳል። ፴ ዳዎን የተረዳ መሪ አለምን በጉልበት አይገዛም። ሀይልን መጠቀም ብዙም ጊዜ በቀላሉ ያመጣል። ጦር በሰፈረበት ቦታ ሁሉ አሜኬላ እና እሾህ ይበቅላል። ከትልቅ ጦርነት በኋላ የሚከተሉት መጥፎ አመታት ናቸው። ጥሩ ጀነራል አላማውን ካሳካ በኋላ ያቆማል — እንጂ አለምን ለመቆጣጠር አይደፍርም። በሀይሉ አይፎክርም፣ አይመካም፣ አይኮራም። የበላይ የመሆን ምኞት የለውም። ይህ ሀይልን ሳይጠቀሙ ውጤትን ማሳካት ይባላል። ከመጠን በላይ ማደግ መበስበስን ማፋጠን ነውና። ይህ የዳዎ መንገድ አይደለም። ስለዚህ ከዳዎ ጋር የሚቃረን በፍጥነት ያልፋል።2 ፴፩ የጦር መሳሪያዎች የጥፋት አገልጋዮች ናቸው። ጥሩ ሰዎች ሁሉም ይጸየፏቸዋል። ስለዚህ የዳዎ ተከታይ በጭራሽ አይጠቀምባቸውም። የጥበብ አገዛዝን የሚቃወሙ ናቸው። እንደ መጨረሻ አማራጭ ነው የሚያያቸው። በጠቢብ ሰው ልብ ውስጥ ሰላም እና ጸጥታ በጣም የተወደደ ነው። ስለዚህ በጦርነት የተገኘ ድል ለእርሱ ደስታ አይሆንም። መሳሪያን ማምለክ — በሰዎች ሞት መደሰት ነው። በሰዎች እልቂት ስትደሰት የምድር ላይ አላማህን አታስታውስም። ሰዎች የገደለን የጦር ሰራዊት በሀዘን ነው መቀበል ያለብህ — በጦርነት የተገኘ ድል ከቀብር ስነስርአት ስለማይተናነስ።3 ፴፪ መሰረታዊው ዳዎ ለአገላለጽ አይመችም። ቀላል እና ረቂቅ ቢሆንም አለም ላይ ማንም አጥብቆ ሊያቆየው አይችልም። ነገስታት እና ጌቶች ቢጠቀሙበት ኖሮ እልፍ አእላፍ ነገሮች በተፈጥሮ መንገድ ይታዘዙላቸው ነበር። ሰማይ እና ምድር በደስታ ይተባበሩላቸው ነበር። ሁሉም ሰው ተስማምቶ የሚኖረው በይፋዊ ድንጋጌ ሳይሆን በራሱ መልካምነት ነው። ሁሉም ሲከፋፈል — ስም መጠቀም መግለጽ አስፈለገ። ያሉት ስሞች በቂ ናቸው። ስለዚህ መሰየምን መቼ ማቆም እንዳለብን እንወቅ። መቼ ማቆም እንዳለብን ማወቅ ራሳችንን ከአደጋ መጠበቅ ነውና። ወንዞች እና ጅረቶች የተወለዱት ከውቅያኖስ ነው። ሁሉም ፍጥረታት የተወለዱትም ከዳዎ ነው። ውሀዎች ሁሉ ተመልሰው ውቅያኖስ እንደሚሆኑ ሁሉ የሁሉም ፍጥረት መመለሻ ደግሞ ዳዎ ነው። ፴፫ ሌሎችን የሚረዳ ሰው — እውቀት አለው። ራሱን የሚያስተውል ሰው — ጥበብ አለው። ሌሎችን የሚያሸንፍ — ጉልበት ይጠይቃል። ራሱን መግዛት ደግሞ — ጥንካሬን ይፈልጋል። በቂ እንዳለህ ማወቅ — ሀብታም መሆን ነው። በዳዎ መንገድ ላይ በጽናት የሚተጋ — የአላማ ሰው ነው። በዘመኑ የሚኖር — ረጅም እድሜ ኖሮታል። በዳዎ ደግሞ የሚኖር — ለዘላለም ይኖራል።4 ፴፬ ታላቁ ዳዎ ሁለንተናዊ ነው። በሁሉም አቅጣጫ መመልከት ይችላል። እልፍ አእላፍ ነገሮች በእሱ ላይ ጥገኛ ቢሆኑም ግን ምንም ሳያስቀር ይረዳቸዋል። ተግባሩን ይፈጽማል — ነገር ግን ምንም ውለታ አይጠይቅም። እልፍ አእላፍ ነገሮችን ይሸፍናል እንጂ እነሱን ለመቆጣጠር አይሞክርም። በሚቆጣጠራቸውም ግን እልፍ አእላፍ ነገሮች ወደ እርሱ ይመለሳሉ። ስለዚህ ታላቅ ተብሎ ሊጠራ ይችላል። ስለዚህ እውነተኛ ታላቅ ሰው መሆንን አይፈልግም — እናም በእውነትም ታላቅ ይሆናል። ፴፭ ታላቁን የዳዎ ቅርጽ አጥብቆ የያዘ እርሱ ሁሉንም ነገር ይስባል። ሁሉም ነገሮች ወደ እርሱ ይጎርፋሉ — ምክንያቱም ዳዎ ውስጥ ሰላም፣ ደህንነት እና ደስታ ስላለ። ሙዚቃ እና ጣፋጭ ምግቦች የሚያልፍ መንገደኛን ለአፍታ ማቆም ብቻ ነው የሚችሉት። የዳዎ ቃላት ግን — ምንም እንኳን ለስላሳ እና ቀለልተኛ ቢሆኑም ምንም እንኳን ለአይንም ወይ ለጆሮም የማይስቡ ቢመስሉም — ጥቅማቸው ግን ዘላቂ ነው። ፴፮ የሚጨማደደው — መጀመሪያ ስለተዘረጋ ነው። የሚደክመው — መጀመሪያ ጠንካራ ስለነበረ ነው። የሚነሳው — ስለተጣለ ነው። የሚወሰደው — ስለተሰጠ ነው። ይህ የተጋረደው ጥበብ ይባላል። ረጋ ያለ ጠንካራ እና ሀይለኛውን ያሸንፋል። አሳ ከጥልቁ ውስጥ እንደማይወጣ ሁሉ የአንድ ሀገር የጦር መሳሪያም ህዝብ ፊት መውጣት የለበትም።5 ፴፯ ዳዎ ምንም አያደርግም — ነገር ግን ምንም ነገርን አይተውም። መሪዎች ዳዎን ማቆየት ከቻሉ ሁሉም ነገር በድንገት ይለወጣል። ሀያላን ሰዎች ዳዎ ላይ ቢያተኩሩ ኖሮ መላው አለም ተፈጥሯዊ ቅላጼ ኖሮት ነበር። ህይወት ቀላል ስትሆን ማስመሰል ይወርቃል። የኛም ተፈጥሮ በብሩህ መልኩ ያበራል። ባለመፈለግ — መረጋጋት አለ። መረጋጋት ደግሞ — አለምን ራሱ ያቃናል። ጸጥታ ሲኖር አንድ ሰው የአጽናፈ ሰማይን መሰረት በራሱ ውስጥ ያገኛል። ፴፰ ከፍተኛ በጎነት ያለው ሰው ስለበጎነት ጠንቅቆ አያውቅም። በዚህም ምክንያት — እውነተኛ በጎነትን ይይዛል። ትንሽ በጎነት ያለው ሰው ደግሞ በጎ ለመሆን ይሞክራል። በዚህም ምክንያት — በጎነት ይጎድለዋል። ከፍተኛ በጎነት ያለው ሰው ጫጫታ አይፈጥርም — ስለዚህ አይታይም። ትንሽ በጎነት ያለው ሰው ደግሞ ሁልጊዜ ጫጫታ ይፈጥራል — ስለዚህም ሁልጊዜ ይታያል። እውነተኛ ጥሩ ሰው — ያለድብቅ አላማ አይሰራም። ስነምግባር ያለው ሰው — የሚሰራው ከግል ምኞቱ ነው። የበላይነት የሚሰማው ሰው ደግሞ እርምጃ ይወስዳል — እና ሰዎች ምላሽ ካልሰጡት እጆቹን ዘርግቶ ያስገድዳቸዋል። ዳዎ ያልተሳካለት ሰው — ወደ በጎነት ይሄዳል። በጎነት ያልተሳካለት ሰው — ወደ ሰብአዊነት ይሄዳል። ሰብአዊነት ያልተሳካለት ሰው — ወደ ምግባር ይሄዳል። ስነምግባር ያልተሳካለት ሰው — ወደ ስነስርአት ይሄዳል። አሁን ስነስርአት ብቸኛው የእምነት እና የታማኝነት ሽፋን ይሆናል። ይህ ደግሞ የሁሉም ውዥንብር እና ብጥብጥ መጀመሪያ ነው። አስቀድሞ ማወቅ የዳዎ አበባ ሊሆን ይችላል — ግን የስንፍና መጀመሪያ ነው። ስለዚህ ታላቁ ሰው በደካማው ሳይሆን በጠንካራው ነገር ላይ ይመሰረታል። በአበባው ሳይሆን — በፍሬው ውስጥ ይኖራል። ስለዚህ አንዱን ጥሎ ሌላውን ይወስዳል።6 ፴፱ ከጥንት ጀምሮ አንድነትን ያገኙ ነገሮች እንከን የለባቸውም። ሰማይ አንድነት ስላለው ነው — ግልጽ የሆነው። ምድር አንድነት ስላገኘ ነው — ጸጥታ የሰፈነው። ከመናፍስት አንድነት ነው — መላእክት የተገኘው። የምንጮቹ አንድነት ነው — ወንዙን የሞላው። እልፍ አእላፍ ፍጥረታትም — አንድነትን አግኝተው ነው የተወለዱት። የህዝብ እና የገዢ አንድነት ነው — የአለምን ሉአላዊነት ያስጠበቀው። ይህ ሁሉ የመጣው ከውህደት ነው። ሰማይ ግልጽ ካልሆነ — ብዙም ሳይቆይ መሰነጣጠቅ ነበር። ምድር ጽኑ ባትሆን ኖሮ — በቅርቡ ታጥፋ ትሰበር ነበር። መናፍስቱ ጠንካራ ባይሆን ኖሮ — ብዙም ሳይቆይ ይደክም ነበር። ሸለቆው ሁሌ ባይሞላ ኖሮ — እስካሁን ደርቆ ነበር። እልፍ አእላፍ ነገሮች ባይባዙ ኖሮ — እስካሁን አይዘልቁም ነበር። መሪዎች መምራት ካልቻሉ — ብዙም ሳይቆይ ይወድቃሉ። ስለዚህ የታላቅነት ምንጭ የሚገኘው ከጥቂቱ ነው። ዝቅተኛው — የከፍተኛው መሰረት ነው። ባለስልጣኖች ብቻቸውን ረዳት የሌላቸው ዋጋቢስ ተብለው ይጠራሉ። ይህ ለዝቅተኛው እውቅና መስጠት አይደለምን? የሰረገላ ክፍሎችን መዘርዘር ሰረገላን መግለጽ አይደለም። ስለዚህ ከፍተኛው ታዋቂነት — ያለ ዝና ነው። እንደ ከበረ ድንጋይ ከብዙዎች አንዱ ለመሆን ከመፈለግ ይልቅ እንደ አለት ጠንካራ ሆኖ መቆየት ጥበብን ይቀጥሳል። ፵ የዳዎ እንቅስቃሴ — መመለስንም ያካትታል። የዳዎ መንገድ — መረታትን ያካትታል። የአለም ነገሮች የሚመነጩት — ከመሆን ነው። መሆን ደግሞ — ካለመሆን ይጀምራል።7 ፵፩ ጥበበኛ ምሁር ዳዎን ሲሰማ በትጋት ይለማመዳል። ተራ ምሁር ዳዎን ሲሰማ በማመን እና ባለማመን መካከል ይከራተታል። የማይረባ ምሁር ዳዎን ሲሰማ በቁጣ ይስቃል። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ሰው ካልሳቀበት ዳዎ ዳዎ አይሆንም ነበር። የጥንት ጠቢባን እንዲህ ብለው ነበር — ብሩህ መንገድ — የደበዘዘ ይመስላል። ወደፊት የሚያስኬደው መንገድ — ወደኋላ የሚመራ ይመስላል። ደልዳላው መንገድ — ወጣገባ ያለው ይመስላል። እውነተኛው ሀይል — ድክመት ይመስላል። ታላቁ ንጽህና — ቶሎ የሚቆሽሽ ይመስላል። እውነተኛ ግልጽነት — የማይታይ ይመስላል። ታላቁ ጥበብ — ያልተወሰሰበ ይመስላል። ታላቁ ፍቅር — ግድየለሽነት ይመስላል። ዳዎ የተደበቀ እና ስምየለሽ ነው። ሆኖም ግን ሁሉንም ለብቃት የሚያቀርበው እና ወደ ፍጽምና የሚያመጣው ዳዎ ብቻ ነው። ፵፪ ዳዎ አንድን ይወልዳል። አንድ ሁለትን ይወልዳል። ሁለት ሶስትን ይወልዳል። ሶስት እልፍ አእላፍን ይወልዳል። እልፍ አእላፍ ይንን በጀርባቸው ተሸክመው ያንግን ከፊታቸው ያደርጋሉ። በሁለቱ ሀይሎች ውህደት አማካኝነት ወደ ስምምነት ይደርሳሉ።8 ረዳት የለሽ፣ ትንሽ እና ከንቱ ከመሆን በላይ በሰዎች ዘንድ የሚጠላ ነገር የለም — ግን እነዚህ መኳንንት እና ጌቶች ራሳቸውን የሚጠሩባቸው ስሞች ናቸው። እውነት ለመናገር — አንድ ሰው በማጣት ሊያተርፍ ይችላል። በማግኘት ሊያጣ ይችላል። ሌላው ያስተማረኝን እደግመዋለሁ — ጠበኛ እና ጨካኝ ሰዎች በተፈጥሮ ሞት አይሞቱም። ይህንን የትምህርቴ መሰረት አድርጌ እወስደዋለሁ። ፵፫ እዚህ አለም ላይ ቀጭቀጭ ያለ ሰው በጣም አስቸጋሪ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ያሸንፋል። አለመሆን — ክፍተት ወይም ስንጥቅ ወደሌለው ቦታ ሳይቀር ሾልኮ ይገባል። ስለዚህ ሳይታገሉ መተግበር ጥቅም እንዳለው አውቃለሁ። ቃላትን የማይጠቀም ትምህርት እና ትግል የሌለው ተግባር — አለም ላይ ካሉት ጥቂት ሰዎች በስተቀር ሌሎች ሊረዱዋቸው የማይችሉት ነገሮች እንደሆኑም አውቃለሁ። ፵፬ ዝናህ ወይስ ሰውነትህ — የትኛው የበለጠ አስፈላጊ ነው? ሰውነትህ ወይስ ንብረትህ — የትኛው የበለጠ ዋጋ አለው? ማግኘት ወይስ ማጣት — የትኛው የበለጠ አሳማሚ ነው? ጠቢቦች እንደሚሉት — የምታገኘው ከምታጣው የበለጠ ችግር አለው። ፍቅር — የመስዋዕትነት ፍሬ ነው። ሀብት — የልግስና ፍሬ ነው። ባለው የሚረካ ሰው — ክፉ አያነካውም። መቼ ማቆም እንዳለበት የሚያውቅ ሰው — ከመከራ የጸዳ ነው። በዚህ መንገድ ብቻ ነው ለረጅም ጊዜ በጥበብ መቆየት የሚቻለው። ፵፭ ታላቅ ስኬት — ያልተሟላ ይመስላል። ሆኖም ግን ጥቅሙ አያልቅም። ትልቅ ሙሉነት — ባዶ ይመስላል። ሆኖም ግን ጥቅሙ ተማጦ አያልቅም። ታላቅ ቅንነት — ጠማማ ይመስላል። ታላቅ ብልሃት — ሞኝነት ይመስላል። ታላቅ አንደበተርቱነት — ግራቢስ ይመስላል። ታላቅ እውነት — ውሸት ይመስላል። እረፍት — እንቅስቃሴን ያሸንፋል። መረጋጋት — ሙቀትን ያሸንፋል። መረጋጋት — የአጽናፈ ሰማይ ቅደም ተከተል ነውና። ፵፮ ዳዎ በአለም ላይ ሲያሸንፍ ፈረሶች እርሻ ቦታቸውን በፍጋቸው እንዲያዳብሩ ይደረጋል። አለም ዳዎ አልባ ስትሆን ግን የጦር ፈረሶች በከተማ ዳርቻዎች ላይ ይራባሉ። ምኞትን አጠንጥኖ ከማስቀመጥ የበለጠ በደል የለም። ከስግብግብነት የበለጠ ጥፋት የለም። ከመጎምጀት የበለጠ መጥፎ እድል የለም። የሚበቃውን የሚያውቅ ብቻ ነው ሁሌም በቂ የሚኖረው። ፵፯ ከበር ሳትወጣ የአለምን መንገድ ማወቅ ትችላለህ። መስኮቱን ሳትመለከት የገነትን መንገድ ማየት ትችላለህ። በራቀ ቁጥር — የምታውቀው ትንሽ ነው። ስለዚህ ጠቢቡ — የትም ሳይሄድ ያውቃል። ሩቅ ሳይመለከት ይረዳል። እና ምንም ሳያደርግ ይፈጽማል። ፵፰ በመማር ሂደት ውስጥ በየቀኑ አንድ ነገር ይጨመራል። በዳዎ ትምህርት ግን በየቀኑ አንድ ነገር ይለቀቃል። ምንም ነገር የማናደርግበት ደረጃ ላይ እስክንደርስ ድረስ ትንሽ ትንሽ እያረግን እንለቃለን። ምንም ነገር የማናደርግበት ደረጃ ላይ ስንደርስ አሁን ምንም አልቀረም። ነገሮች በራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ በማድረግ እውነተኛ ጥበብ ማግኘት ይቻላል። ሁልጊዜ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ግን አለምን ለማሸነፍ በቂ አይሆንም።9 ፵፱ ጠቢብ የራሱ ፍላጎት የለውም — ግን የህዝብን ጥቅም የራሱ አድርጎ ይወስዳል። እሱ ለደግ — ደግ ነው። ደግ ላሉትም — ደግ ነው። ደግ መሆን በጎነት ነውና። እሱ ለታማኞች — ታማኝ ነው። ለከዳተኞችም — ታማኝ ነው። መታመን በጎነት ነውና። ጠቢቡ ከሰማይ በታች ካሉት ጋር ሁሉ ተስማምቶ ይኖራል። ሁሉንም ነገር እንደራሱ አድርጎ ይመለከታል። ሁሉም ሰዎች ወደ እሱ ይሳባሉ — እሱም እንደልጆቹ ይንከባከባቸዋል። ፶ ወደ ህይወት ከመጣን ወደ ሞት እንመለሳለን። ከአስሩ ሶስቱ — የህይወት አጋሮች ናቸው። ከአስሩ ሶስቱ — የሞት ባልደረቦች ናቸው። ነገር ግን ሰዎች ህይወትን ብቻ ስለሚያዩ በሁሉም ተግባራታቸው ወደ ሞት ግዛት ይሄዳሉ። ለምን ይሄ ሆነ? ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በጣም የመኖር ጉጉት ስላላቸው ነው። የራሱን ህይወት በመጠበቅ የላቀ ብቃት ያለው ሰው — መሬት ላይ ሲጓዝ አውራሪስ ወይም ነብር አይነካውም። ጦርነት ውስጥ ራሱ የጦር መሳሪያ አይነካውም — ሲባል ሰምቻለሁ። አውራሪስ — ቀንዱን የሚያሳርፍበት ቦታ የለም። ነብር — ጥፍሩን የሚያስቀምጥበት ቦታ የለም። መሳሪያውም — ምላጩን የሚያሳርፍበት ቦታ የለም። ይህ ለምን ሆነ? ምክንያቱም ሞት የሚገባበት ቦታ ስለሌለው።10 ፶፩ ዳዎ ለሁሉም ነገር ህይወት ይሰጣል። በበጎነቱ ይመግባቸዋል። እያንዳንዱን ነገር እንደ ተፈጥሮው ይመሰርተዋል። ሁኔታዎችንም ወደ ብስለት ያመጣቸዋል። ስለዚህ እልፍ አእላፍ ፍጥረታት ሁሉ በተጋት መንገዱን ያከብራሉ። ይሁን እንጂ መንገዱ በተጋት የተከበረው በየትኛውም ባለስልጣን ስለተደነገገ አይደለም — መከበራቸው ተፈጥሯዊ ስለሆነ ነው እንጂ። ስለዚህ ዳዎ ለሁሉም ነገር ህይወት ይሰጣል — በበጎነቱ ያሳድጋቸዋል፣ ይመግባቸዋል፣ ወደ ሙሉ እድገታቸውም ያመጣቸዋል። ስልጣንን ሳይጠይቁ ህይወት መስጠት፣ ምስጋናን ሳይጠይቁ ጠቃሚ መሆን፣ ያለቁጥጥር መምራት — ይህ ድብቅ በጎነት ይባላል። ፶፪ ከሰማይ በታች ያሉ ነገሮች ሁሉ አንድ ጅምር ነው ያላቸው። እና ያ ጅምር — የሁሉም ነገሮች እናት ተብሎ ሊጠራ ይችላል። የሁሉንም ነገሮች እናት ስታውቅ ልጆቹንም አብረህ ታውቃለህ። ስለዚህ ልጆቹን እወቅ — ግን እናታቸውን አጥብቀህ ያዝ። እስከ ዘመንህ መጨረሻ ድረስ ከአደጋ ነጻ ትሆናለህ። አፍህን ተቆጣጠር — ስሜትህን ጠብቅ — እና ህይወትህ ሁሌ ስራ በዝቶባት ተስፋ ታጣለች። አፍህን ክፈት — ህይወትህ ሁሌ ስራ በዝቶባት ተስፋ ታጣለች። ትንሽ ማየት — ግልጽነት ይባላል። ተለዋዋጭነትን መጠበቅ — ጥንካሬ ይባላል። ደማቁን ጸብራቅ በመጠቀም ወደ ብርሃንህ ተመለስ። ራስህን ከመከራ አድን። ይህ የዘላለምን ብርሃን የምናገኝበት ልምምድ ነው። ፶፫ ትንሽ እንኳን የመረዳት ፍቃድ ካለኝ በታላቁ የዳዎ መንገድ መሄድ አለብኝ። እና የኔ ፍርሃት መሆን ያለበት ከዳዎ መንገድ መራቅ ብቻ ነው። ይህ ታላቅ መንገድ ቀጥተኛ እና የረጋ ነው። ሆኖም ግን ሰዎች ብዙውን ጊዜ የርጥባን መንገድ ይመርጣሉ። ለዚህም ነው — ፍርድ ቤቱ በምስና የተዘፈቀው። እርሻው በአረም የተሞላው። ጎተራው ባዶ የሆነው። በሚያምር መልኩ መልበስ፣ ስለታም ጎራዴ መታጠቅ፣ በምግብ እና በመጠጥ ራስን ማምራት፣ ምን እንደምናደርገው እስከማናውቀው ድረስ ሀብትን ማካበት — የዘራፊዎች ባህሪን ማንጸባረቅ ነው። ይህ በእርግጥ ከዳዎ መንገድ በጣም የራቀ ነው። ፶፬ በዳዎ ውስጥ የተተከለው — አይነቀልም። ዳዎ ያቀፈውን — አያሸራትትም። ሲወርድ ሲዋረድ ይቆያል። በዘላቂነቱም ይከበራል። በጎነትን በራስህ ማንነት አዳብር — እና ያንተ እውነተኛ ካል ይሆናል። በቤተሰብ ውስጥ ስታዳብረው — ጸንቶ ይኖራል። በማህበረሰብ ውስጥ ስታሳድገው — ሁሌም ይኖራል። ሀገር ውስጥ ስታለማው — በብዛት ይበቅላል። በአለም ውስጥ ስታዳብረው ደግሞ — ሁለንተናዊ ይሆናል። ስለዚህ ሌሎችን ከራስህ ጋር አስተያይተህ ተመልከት — ሰውን እንደ ሰው ተመልከት። ቤተሰብን እንደ ቤተሰብ። ማህበረሰብን እንደ ማህበረሰብ። ሀገርን እንደ ሀገር። አለምን እንደ አለም። ይህ የእውነት መንገድ መሆኑን እንዴት አውቃለሁ? ውስጤ ያለውን በማየት።
ማስታወሻዎች
Footnotes
ዳዎ ዴ ቺንግ ምዕራፍ ፩ — የዳዎ ተፈጥሮ ሊነገር እንደማይችል የሚያስረዳው ታዋቂ መክፈቻ። Cf. Laozi, Tao Te Ching, trans. Stephen Mitchell (Harper Perennial, 1988), ch. 1. ↩
ምዕራፍ ፫ — ውዝዋዜ ያለበት ምዕራፍ ሲሆን “ህዝቡን ከእውቀት ማራቅ” የሚለው ሀሳብ በብዙ ተርጓሚዎች ዘንድ እንደ ፖለቲካዊ ሴራ ሳይሆን ከማይጠቅም ኢንቴሌክቹዋል ትዕቢት ማራቅ ተብሎ ይተረጎማል። Cf. D.C. Lau, Lao Tzu: Tao Te Ching (Penguin, 1963), notes to ch. 3. ↩
ምዕራፍ ፮ — “ሚስጥራዊቷ እንስት” (谷神 / 玄牝) በቻይንኛ ፍልስፍና ውስጥ የፈጠራ ምንጭን የሚወክል ተምሳሌት ነው። ↩
ምዕራፍ ፰ — ውሀ ከዳዎ ጋር የሚያመሳስለው ማስመሰል ከዳዎይዝም ማዕከላዊ ምስሎች አንዱ ነው። Cf. Ursula K. Le Guin, Lao Tzu: Tao Te Ching — A Book about the Way and the Power of the Way (Shambhala, 1997), ch. 8. ↩
ምዕራፍ ፲ — “ድብቅ በጎነት” (玄德 xuándé) የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ በምዕራፍ ፲፣ ፶፩ እና ፶፭ ውስጥ ይደጋገማል። ↩
ምዕራፍ ፲፯ — በደረጃ ስለተቀመጡ አራት የአመራር ዓይነቶች የሚያስረዳ ምዕራፍ። ከሁሉ የላቀው ህዝቡ ያሉትን እንደ ተፈጥሯዊ የሚቆጥረው ዓይነት ነው። ↩
ምዕራፍ ፳፭ — “ዳዎ ተፈጥሮን ይከተላል” (道法自然) — ዳዎ ራሱ ከሁሉ በላይ ነው ግን ራሱን ከተፈጥሮ ስርአት ጋር ያስማማል። Cf. Wing-tsit Chan, A Source Book in Chinese Philosophy (Princeton University Press, 1963), p. 153. ↩

